የሰብል ልማት ትምህርት ክፍል በኮሌጁ ካሉት የት/ት ክፍሎች አንዱ ሲሆን በየዓሜቱ በርካታ በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት መርሀ-ገብር ሰልጣኞችን በመቀበል እያሰለጠነ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም የመማር ማስተማር ተግባራት እና በሌሎችም ከት/ት ክፍሉ ጋር ግንኙነት ባላቸው ተግባራት በመሳተፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ በ2016 በጀት ዓሜትም የተለያዩ የመማር ማስተማር ስራዎችን ለማከናወን በቂ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን በክፍሉ ውስጥ ያሉ 28 መምህራንና 2 ቴክኒካል ረዳቶች በጠቅላላ 30 የሰው ሃይል ያላቸውን ዕውቀት ክሂሎትና ሙያ በሙሉ በማስተባበር ወደ ሥራ  ገብተናል፡፡

ዓላማ፤

በበጀት ዓሜቱ በኮለጁ በኩል ለት/ት ክፍሉ የሚደለደሉ ነባርና አዲስ የመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብር ተማሪዎችን በመቀበል ተገቢውን የተግባርና የጽንሰ-ሐሳብ ት/ቶችን በተገቢና በጥራት በመስጠት እንድሁም የተለያዩ የት/ት መርጃ መሣሪያዎችን በማዘጋጀትና  የት/ት አሰጣት ዘዴዎችን በማዘመን ብቁና ተወዳዳሪ ሥልጣኞን ማፍራት ብሎም ኮሌጁን በሰብል ልማት ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥለዋል፡፡ ከመማር ማስተማር ሥራ ጎን ለጎን የተለያዩና ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምርና ፕሮጄክት  ሥራዎችን በማከናወን ተገቢውን የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠትና ባለ ድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተጠቃሚና ተሳታፊ እንድሆኑ ማድረግ ሥራ እየተሠራ ይገኛለል፡፡

ዋና ዋና ተግባራት

  1. የመማር ማስተማር ቅድመ ዝግጅት፤
  2. የመማር ማስተማር ሥራዎችን ማከናወን
  3. የተግባር ትምህርት ማሳና ቤተሙከራ ማደራጀት
  4. ቬርሚ ኮምፖሰት ማምረት እና ለሽያጭ ማቅረብ ተጀመረዋል
  5. ሁሌገብ ችግኝ ጣቢያ ላይ አቦካዶና ቡና ዘር ተተክለዋል
  6. ሥራሥር ሰብል ማሳ ላይ ስ/ድንች፣ካሳባ፣እንሰትና ጎዳሬ ማንከባከብ ተችለዋል
  7. የቀናጀ ቨርቲካል ፋርሚንግ፣ ቤተ ሙከራ ቤት ማደራጀት
  8. ጥምር የከተማ ግብርና በአድስ መልክ  ማሳዳስ ሥራ እተሠራ ይገኛል
  9. ለፋርም ሥራዎች ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ
  10. ፍራፍሬ ማሳ ለይ ያረጁ አቦካዶ፣ፓፓያ ና ሙዝ መስነሳት፣ከተሸሻሉ ዝርያ ፣ ለመትከል 
  11. ጓሮ አተክልት 
  12. በእፀዋት ማዕከል(Botanical Garden) ማሳደስ
  13. ሥራሥር(ስኳር ድንች፣ድ/ድንች፣እንሰትና ካሳሳባ  ሰብል ማሳ ላይ ድጋፊ ተመርተዋል
  14. ሁሌገብችግኝ ጣቢያ- ሙያዊ ድጋፍ
  15. የአቅም ግንባታሥራዎችን መሥራት

ነባር እና አዳዲስ የምርምር፣ሥርፀት እና ፕሮጀክት ሥራዎችን መደገፍ

የቨርሚ ኮምፖስት የሥራ ክንውን ሪፖርት

የሰብል  ልማት  ትምህርት  ክፍል 2017 ለአጫጭር ስልጠና  ለመስጠት  የተመረጡ  ሙያ  ዓይነቶች፤

1)         Fruit and vegetable or Agro-food food processing

2)         Prepare compost or Vermicompost

3)         Fruit propagation

4)         Spray Service Provider or Pesticide Application Service

5)         Vegetable producer መሆናቸዉን እንገልፃለን፡፡

ትምህርት ክፍልት/ት ደረጃ ጠቅላላ ድምር
ሰብል ልማትመጀመሪያ ዲግርየሁለተኛ ዲግርድፕሎማ
   
4151832111225530