SNV Project

የኤስ ኤን ቪ ፕሮጀክት ክልላዊና አገር አቀፍ ደረጃ አስተባባሪዎችን ጨምሮ ከኒዘርላንድ ኢምባሲ የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ወደ ኮሌጃችን በመምጣት ውይይትና መስክ ምልከታ አካሄደ።
ወ/ሶ/ግ/ኮ ጥር 06/2017 ዓ/ም

የኤስ ኤን ቪ (SNV) ፕሮጀክት ክልላዊና አገር አቀፍ ደረጃ አስተባባሪዎችን ጨምሮ ከኒዘርላንድ ኢምባሲ የተውጣጣ ልዑካን ቡድን ወደ ኮሌጃችን በሆርቲ ላይፍ ፕሮጀክት ታቅደው የተሰሩ ሥራዎችን በሚመለከት ውይይትና መስክ ምልከታ አደርጓል።

ልዑካን ቡድኑ ውይይትና መስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅትም ፣ኮሌጃችን ከፕሮጀክቱ ጋር በመቀናጀት በተማሪዎች ማሳ፣ በሥርዓተ ጾታ፣በአቅም ግንባታና በሌሎች ዘርፎች ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ገለጻ ተደርጓል።

ልዑካን ቡድኑ በተማሪዎች ማሳ ላይ በሰብል ልማት ትምህርት ክፍል ተማሪዎች እየተሰሩ ያሉ የእርሻ ልማት ሥራዎችንና ሽቅብ ግብርና በመጎብኘት መስክ ምልከታ አድርጓል።

በማጠቃለያው ላይ አስተያየት የሰጡ የልዑካን ቡድኑ አባላት፣ ከውይይቱና መስክ ምልከታው ብዙ ልምድ እንዳገኙና ኮሌጃችን እንዴት ከፕሮጀክቱ በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ መመልከት መቻላቸውንና ያዩት ነገር እጅግ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል ።

የኮሌጃችን ዲን ዶ/ር አሉላ ታፈሰ በማጠቃለያው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ፕሮጀክቱ የሰራው ሥራ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን በመጥቀስ፤ ፕሮጀክቱ ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

ዲኑ አክለውም፣ በፕሮጀክቱ የተሰሩ ሥራዎች የማዝለቅና በሌሎች ዘርፎችም የማስፋት ሥራ በኮሌጃችን እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *