የተፈጥሮ ሃብት ልማት ት/ክፍል በኮሌጃችን ከ1994 ዓ/ም ጀምሮ በ10+3 ዲፕሎማ መርሃ-ግብር ሥልጠናን እየሰጠ የኮሌጃችን፣ የክልላችን አልፎም ደግሞ የአገሪቱን ራዕይ እና ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለ ትምህርት ክፍል ነው፡፡

ትምህርት ክፍሉ ከዚህም ባለፈ የዜጎችን የሥራ አጥነት ችግርን የቀረፈ ከመሆኑም ባለፈ የግል ባለኃብቶችን በብዙ የሙያ መስኮች ያፈራ እና ያበቃ ሲሆን ለአብይነትም በውበት ዛፎች ችግኝ ጣቢያ መስራቾችን፣ በተለያዩ የደን እና የቡና ችግኝ ማፍላት ተግባራት የተሰማሩትን፣ የደን ዘር አሰባሰብ እና አቅራቢ የግል እና ማኅበራትን፣ በውሃ አሰባስብ፣ አጠቃቀም እና አያያዝ በማስተካከል ምርትና ምርታማነትን በሚያሻሽሉ ተግባራት እንዲሰማሩ በማድረግ በርካታ ችግሮችን ከፈታባችው የሥልጠና መስኮች አንዱ መሆኑ ይታመንበታል፡፡

ከዚህም ባሻገር ሙያው ሠልጣኞች ወደ ተለያዩ የሥልጠና እና የሙያ ማሻሻያ ደረጃ እንዲገቡ መንደርደሪያ በመሆን ያገዘ፣ በአገሪቱ የፖሌቲካ ምህዋር በመሳተፍ ትልቅ ለውጥ እንዲመጣ የበኩሉን ድርሻ ያሳየበት፣ በመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በመሰማራት ውጤታማ እና አኩሪ ልማት ለአገሪቱ ያመጡ ዜጎች ያፈራ መሆኑን በጥናት የተረጋገጠ ቁጥር ማስቀመጥ በይቻልም አሁን እያየን ያለንበት ሀቅ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በመምህራን ይዘት ትምህርት ክፍሉ ባሁኑ ጊዜ በቁጥር አስራ አንድ (11) የሙሆኑ ወንድ መምህራን በሁለተኛ ድግሪ፣ በስድስት (6) ወንድ እና አንድ (1) ሴት በድምሩ በሰባት (7) መጀመሪያ ድግሪ በያዙ እና አሁን በትምህር ላይ ያሉ በቁጥር አራት (4) ወንድ እና አንድ (1) ሴት በድምሩ አምስት (5) በደረጃ 4 የተመረቁ ቴክንክ ረዳቶችን በመያዝ የተዋቀረ ነው፡፡

የሚከናወኑ ተግባራት፡ – የመማር ማስተማሩ ሥራ የትህርት ክፍሉ ዓብይ ተግባር ሲሆን ይህንን ተግባር ለማሳለጥ በተግባር እና በንድፈ-ሃሳብ የበቁ ሠልጣኞችን ለማፍራት ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡

  • የማስተማሪያ ጥራዞችን ይከልሳል ክፍተቶችን በጋራ በማረም ጥራቱን የጠበቀ ማስተማሪያ ጥራዝ ያዘጋጃል
  • በየጊዘው የማስተማሪያ ዕቅድ እና የምዘና ዕቅድ ከሥልጠና በፊት ያዘጋጃል
  • ለመውጫ ፈተና ሊያዘጋጅ የሚችል የትምህርት ክፍሉን ምሳሌያዊ ፈተና () በማውጣት በእውቀትና ክፍሎት ሠልጣኞች ያበቃል
  • የመምህራንን አቅም ወቅቱን በሚመጥን መሠረት ክህሎት ክፍተታቸውን እየለየ የሙያ ማሻሻያዎችን ሥልጠና በመስጠት አቅማቸውን ይገነባል
  • የሠልጣኞች ተግባር ሥልጠና ቦታዎችን የደራጃል ለሥልጣኞችም ሚቹ ያደርጋል
  • የምርምር እና ፕሮጀክት ተግባራትን ያከናውናል፡፡

በአሁኑ ወቅት ትምህርት ክፍሉ በመደበኛው መርሃ-ግብር በቁጥር 181 ወንድ 103 ሴት በድምሩ 284 በደረጃ ሶስት ሠልጣኞችን እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ ከመደበኛው ባሻገር በተከታታይ መርሃ-ግብር በደረጃ አንድ ወንድ 58፣ ሴት 50 በድምሩ 108 ሲሆን በደረጃ ሶስት ወንድ 124፣ ሴት 153 በድምሩ 277 እያሠለጠነ ይገኛል፡፡