የኮሌጃችን ሦስተኛ ዓመት ተፈጥሮ ሀበት አያያዝ መደበኛ መርሐ-ግብር ተማሪዎች ወደ ሶዶ አፈር ምርመራ ቤተ-ሙከራ በመሄድ የተግባር ልምምድ አደረጉ፡፡
ወ/ሶ/ግ/ኮ ታህሳስ 18 2017 ዓ.ም
የኮሌጃችን ሦስተኛ ዓመት ተፈጥሮ ሀብት አያያዝ መደበኛ መርሐ-ግብር ተማሪዎች ወደ ሶዶ አፈር ምርመራ ቤተ-ሙከራ በመሄድ በመሄድ የተግባር ልምምድ አድርገዋል፡፡
ተማሪዎቹ የአፈር ሦሰቱ ባህሪያት ላይ ማለትም በአካላዊ፣ኬሚካላዊና ሥነ-ህይወት ባህሪያት ላይ የተግባር ልምምድ አድርገዋል፡፡
የተግባር ልምምዱ ኮሌጃችን የሚከተለውን 70/30 የሥልጠና ሞዳሊቲ ለማሳለጥ በኮሌጅ ውስጥ ከሚሰጥ ንድፈ-ሃሳብና ተግባር ልምምድ በተጨማሪ ተማሪዎች በአከባቢ ወደ ሚገኙ ተቋማት በመሄድ እየወሰዱ የሚገኙት የትብብር ሥልጠና አካል ነው፡፡