የኮሌጃችን እንስሳት እርባታ ት/ት ክፍል ሦስተኛ ዓመት መደበኛ መርሐ-ግብር ተማሪዎች እንስሳት ድርቆሽ መኖ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ላይ የተግባር ልምምድ ማድረጋቸው ተገለጸ።
የኮሌጃችን እንስሳት እርባታ ት/ት ክፍል ኃላፊ መ/ር ዘፍኔ ኦኑ፣ የትምህርት ክፍሉ ሦስተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በእንስሳት ድርቆሽ መኖ አዘገጃጀትና አጠቃቀም ላይ የተግባር ልምምድ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
መ/ር ዘፍኔ አያይዘውም፣ በአከባቢው ብሎም በክልሉ ዝናብ በሚዘንብባቸው ወቅቶች አረንጓዴ መኖው የመትረፍረፍ እንዲሁም በበጋው ወቅት ደግሞ ለእንስሳት ሰውነት መጠበቂያ የሚሆን መኖ እጥረት እንደሚያጋጥም በማስረዳት፤ የተግባር ልምምዱ ዓላማ ችግሩን ለመቅረፍ እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል ተማሪዎቹ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና የራሳቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።