Animal Health

የእንስሳት ጤና ትምህርት ክፍል በሚያዝያ 2014 ዓ/ም ተከፍቶ በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት መርሀ-ግብር ሠልጣኞችን በመቀበል እያሰለጠነ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡በዚህም የመማር ማስተማር ተግባራት እና በሌሎችም ከት/ት ክፍሉ ጋር ግንኙነት ባላቸው ተግባራት ማለትም የበሽታ ልየታ ምርመራና ህክምና እንዲሁም በሽታ መከላከል፣ እንስሳት ማዳቀል እና ሥጋ ምርመራ ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል፡፡ ትምህርት ክፍሉ ከተከፈተ ጀምሮ በመደበኛ 167 እንዲሁም በተከታታይ ት/ት መርሃ-ግብር 162 በድምሩ 329 ሠልጣኞች በስኬት አስመርቋል፡፡ በ2018 በጀት ዓመትም የተለያዩ የመማር ማስተማር ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን በክፍሉ ውስጥ ያሉ መምህራኖችም ያላቸውን ዕውቀት ክህሎትና ሙያ በሙሉ በማስተባበር ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ይሆናል፡፡ትምህርት ክፍሉ ነባር በመደበኛ መርሃ ግብር 287 እንዲሁም በተከታታይ ት/ት መርሃግብር 314 በድምሩ 601 ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡ እንዲሁም በመደበኛ 3 እና በተከታታይ 4 በድምሩ ለ7 ሴክሺን የእንስሳት እርባታ ተማሪዎች በትምህርት ክፍሉ የሚሰጡ የብቃት አሃዶችን የሚያስተምር ሲሆን በተጨማሪም በ2019 ት/ት ዘመን በመደበኛ (50 ደረጃ 4 እና 50 በመጀመሪያ ዲግሪ) እንዲሁም በተከታታይ ት/ት መርሃግብር (ሳምንት መጨረሻ 150፣ 100 ክረምት)  በድምሩ 350 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

የሠልጣኝ መረጃ በሰንጠረዥ

የገቡበት ዓመትመደበኛተከታታይ
20183911509351144
2017114271415953112
20167125966247109
20155626828247129
የተመረቁ1145316710656162

የሰው ኃይል መረጃ

ት/ት ዝግጅትወንድሴትድምርምርመራ
MSc+ DVM44 
BVSc414 
Level IV11 
Store keeper11 
Total10