የእንስሳት ጤና ትምህርት  በሚያዝያ 2014 ዓ/ም ተከፍቶ በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት መርሀ-ግብር ሰልጣኞችን በመቀበል እያሰለጠነ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም የመማር ማስተማር ተግባራት እና በሌሎችም ከት/ት ክፍሉ ጋር ግንኙነት ባላቸው ተግባራት ማለትም የበሽታ ልየታ ምርመራና ህክምና እንዲሁም በሽታ መከላከል፣እንስሳት ማዳቀል እና ስጋ ምርመራ ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል፡፡ ትምህርት ክፍሉ ከተከፈተ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በመደበኛ 86 እንዲሁም በተከታታይ ት/ት መርሃ-ግብር 31 በድምሩ 117 ሠልጣኞች በስኬት አስመርቋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመትም የተለያዩ የመማር ማስተማር ስራዎችን ለማከናወን በቂ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን በክፍሉ ውስጥ ያሉ 7 መምህራን፣1 ቴክኒካል ረዳት፣ 1 ቻይናዊ መምህር እና 1 መሳሪያ ያዥ በጠቅላላ 10 የሰው ሃይል ያላቸውን ዕውቀት ክህሎትና ሙያ በሙሉ በማስተባበር ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ ትምህርት ክፍሉ ነባር በመደበኛ መርሃግብር 178 እንዲሁም በተከታታይ ት/ት መርሃግብር 238 በድምሩ 416 ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በመደበኛ 5 እና በተከታታይ 5 በድምሩ ለ9 ሴክሺን የእንስሳት እርባታ ተማሪዎች በትምህርት ክፍሉ የሚሰጡ የብቃት አሃዶችን እያስተማረ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም በ2017 ት/ት ዘመን በመደበኛ 150 እንዲሁም በተከታታይ ት/ት መርሃግብር 150 በድምሩ 300 አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

የሠልጣኝ መረጃ በሰንጠረዥ

ዝርዝርመደበኛተከታታይ
ደረጃ 
አንድ150150
ሁለት7125966247109
ሶስት5626828247129
አራት
የተመረቁ59278625631

የሰው ሀይል መረጃ

ት/ት ዝግጅትወንድሴትድምርምርመራ
DVM+MSc33 
MSC11 
Senior Surgeon11Chinese
BVSc33 
Level IV112