
የኮሌጃችን አመራሮች ኦቶና ሆስፒታል መልሶ ለማደራጀት የክልሉ መንግስት ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ድጋፍ አደረጉ። አንጋፋው የኦቶና ሆስፒታል በቀን 19/11/2017 ዓ/ም ባጋጠመው የእሳት አደጋ ምክንያት የንብረት ውድመት መድረሱ ይታወሳል። ይህንን ተከተሎ ሆስፒታሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሟላ አገልግሎት መስጠት እንዲችል መልሶ ለማደራጀት ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ድጋፍ እንዲያደርግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባቀረበው ጥሪ መሰረት የኮሌጃችን አመራሮች ድጋፍ አድርገዋል።