
ኮሌጃችን በትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያ ዓመት ክረምት ትምህርት መርሐ-ግብር ተማሪዎችን መልምሎ ለመቀበል የመግቢያ ፈተና ሰጠ።
ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 10/2017 ዓ/ም
በ2017 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዓመት ክረምት መርሐ-ግብር ለመማር ያመለከቱ ተማሪዎችን መልምሎ ለመቀበል የመግቢያ ፈተና ተሰጥቷል።
የኮሌጃችን ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊና ም/ዲን አቶ ታሪኩ ጨመረ በፈተናው ማስጀመሪያ ላይ ለተፈታኞቹ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኮሌጃችን የትምህርት ጥራት ማዕከል አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ በዚህ መነሻ የመጀመሪያ ዓመት በመደበኛና ተከታታይ ትምህርት መርሐ ግብሮች ተማሪዎችን መልምሎ ለመቀበል የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥና የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን እንደሚቀበል አስታውቀዋል።
ኮሌጃችን ለግብርና ክፍለ-ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱና እያበረከቱ ያሉ ባለሙያዎችን ያፈራ አንጋፋ ተቋም መሆኑን ተናግረው፤ በዘርፉ ልምድ ያካበቱ መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞች፣ ሰፊ ማሳ፣የተደራጁ ቤተ-ሙከራዎችና ሌሎች መሰረተ-ልማቶች እንዳለው አብራርተዋል።



