
የኮሌጃችን አካዳሚክ ኮሚሽንና ማኔጅመንት አባላት በክልላዊ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ላይ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።
ወ/ሶ/ግ/ኮ ሀምሌ 24/2017 ዓ/ም
የኮሌጃችን አካዳሚክ ኮሚሽንና ማኔጅመንት አባላት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ሁምቦ ወረዳ ሶልኳ ተራራ በተካሄደው ክልላዊ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ተራራው ከዚህ ቀደም የጎርፍና ናዳ አደጋ ያጋጠመበት መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን ፣ያ ታሪክ ችግኝ በመትከልና በመንከባከብ ተቀይሮ፣የናዳና ጎርፍ ምንጭ መሆኑ ቀርቶ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር የቱሪዝም ማዕከል እንዲሆን የአከባቢው ማህበረሰብና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው ጥሪ ቀርቧል።
በማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣በምክትል ር/መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሪሁን ፍቅሩንና የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረ/ፕ ሳሙኤል ተሰማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ተግኝተዋል።




